Marathon Motor Engineering plc Ethiopia

Marathon Motor Engineering plc Ethiopia Authorized Hyundai Importer to Ethiopia.

26/05/2026
በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው ሀንዳይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሞዴል ለገበያ ቀረበቢዝነስ  ፅዮን ታደሰ -   ሪፖርተር ጋዜጣ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 -  April 22, 2026ማራቶን ሞተር ...
23/04/2026

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው ሀንዳይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሞዴል ለገበያ ቀረበ

ቢዝነስ ፅዮን ታደሰ - ሪፖርተር ጋዜጣ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 - April 22, 2026

ማራቶን ሞተር ኢንጂነሪንግ በአፍሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ የመጀመሪያ የሆነውን የሀንዳይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡ ማራቶን ሞተር ኢንጂነሪንግ ሚያዚያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም. ‹‹ሀንዳይ አዮኒክ ዘጠኝ ፍላግሽፕ›› የተሰኘ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሞዴል ለዕይታ ያቀረበ ሲሆን፣ ይህም የሀንዳይ የመጨረሻ ሞዴል
መሆኑን የኩባንያው መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መልካሙ አሰፋ ገልጸዋል፡፡
‹‹እስካሁን በመካከለኛው ምሥራቅና በአፍሪካ ይህን ሞዴል በማቅረብ የመጀመሪያዎቹ ነን፤›› ያሉት አቶ መልካሙ፣ አዲሱ ሞዴል ከፊት ለፊቱ 70 ከኋላው 160 በአጠቃላይ 230 የፈረስ ጉልበት
ያለው መሆኑንና አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ ከ850 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት መጓዝ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡
የተሽርካሪው ቁመት ከአምስት ሜትር በላይ መሆኑንና ይህን እስካሁን ካሉት የሀንዳይ ሞዴሎች ረዥምና ግዙፍ እንደሚያደርገው ጠቁመዋል፡፡ ማራቶን ሞተርስ ኢንጂነሪንግ ሁሉንም
ተሽከርካሪዎችን እያስመጣ የሚገጣጥመው ከደቡብ ኮሪያ ኩባንያ ሀንዳይ መሆኑን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀንዳይ የሚያቀርባቸው ተሽከርካሪዎች ባላቸው ከፍተኛ ጥራት የታወቀ ነው ብለዋል፡፡
ማራቶን ሞተርስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለገበያ በማቅረብ ቀዳሚ መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ ከስድስት ዓመታት በፊት ኩባንያው ያቀረባቸውን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች
በመሰብሰብ የባትሪያቸውን ጤና ፍተሻ መደረጉን፣ የሁሉም ተሽከርካሪዎች የባትሪ ጤናማነት መቶ በመቶ ሆኖ መገኘቱን፣ ለዚህም ለደንበኞች አያያዝ የባትሪው ጥራት ምክንያት መሆኑን
አስረድተዋል፡፡
አዲሱን ሞዴል ተሽከርካሪ በምን ያህል መጠን ገበያ ውስጥ ይገኛል ለሚለውና ዋጋውን በሚመለከት ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹የእኛ የማምረት አቅም በብዙ አሥር ሺዎች በመሆኑ የአቅርቦት ችግር
የለብንም፤›› በማለት፣ ተሽከርካሪዎቹ የቀረቡበት ዋጋም 20 ሚሊዮን ብር እንደማይደርስ፣ ዋጋው ከተሽከርካሪው ሁኔታ አኳያ ተመጣጣኝ ለመሆኑ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ
ሲገባቡ የሚከፈለው ቀረጥ ዝቅተኛ መሆኑ እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡

We are pleased that our Company Marathon Motor is awarded Platinum as a High Loyal Tax Payer, for the 2017 E.C. budget y...
08/10/2025

We are pleased that our Company Marathon Motor is awarded Platinum as a High Loyal Tax Payer, for the 2017 E.C. budget year, by Ministry of Revenues and Customs Commission, on October 7, 2025.
Mr. Melkamu Assefa, Founding CEO & MD of Marathon Motor received the award from H.E. Prime Minister Dr. Abiy Ahmed.

Marathon Motor is highly grateful to it’s beloved customers, hardworking staffs and all strategic partners for enabling us achieve this important milestone.

Address

Saris Abo
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 12:00

Telephone

+251966801172

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Marathon Motor Engineering plc Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share