መሐመድ ሁሴን ዓመታዊ የመኪና ምርመራ / Mohammed Hussein annual car inspection

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • መሐመድ ሁሴን ዓመታዊ የመኪና ምርመራ / Mohammed Hussein annual car inspection

መሐመድ ሁሴን ዓመታዊ የመኪና ምርመራ / Mohammed Hussein annual car inspection come to our friendly centre and you will get the best service

04/07/2022
20/06/2022

13/10/2014 ዓ.ም
ኮድ 2 ሠሌዳ ! በተመለከተ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን
በአዲስ አበባ ከሚንቀሳቀሱ አ.አ ሠሌዳ መካከል የኮድ 2 ሠሌዳ አቅርቦት ከትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር በውክልና የወሰደው የፐፕሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በግብዓት እጥረት ምክንያት ለወራት አቅርቦቱ መቋረጡ ይታወቃል፡፡
የገጠመውን የአቅርቦት ችግር በመቅረፍ የምርት ስራው ስለተጀመረ ኮድ 2 አዲስ ሠሌዳ ፈላጊዎች ከ14/10/2014ዓ.ም ጀምሮ ማሟላት ያለባችሁን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት በ11 ቅ/ጽ ቤቶች በመኖሪያ አድራሻችሁ አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያሳውቃል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን

09/03/2022
28/01/2022

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ(ማስክ) ያላደረጉ አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች 1 ሺሕ ብር እንደሚቀጡ ተነገረ፡፡

የኮቪድ 19 ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ በትራንስፖርት ዘርፍ የተቀመጠውን መመሪያ ተግባራዊ በማያደርጉ አሽከርካሪዎች ላይ ከአርብ ጀምሮ ቁጥጥር እንደሚደረግ ያስታወቀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ነው፡፡

ቢሮው የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት የተሽከርካሪዎችን ንጽህና መጠበቅ፣ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች ማስክ መጠቀም እንዲሁም ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪዎች አገልግሎት እንዳያገኙ ማድረግ እንደሚገባ አብራርቷል፡፡

የኮቪድ ስርጭት ለመግታት በወጣው መመሪያ መሰረት ማስክ ያላደረጉ አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች ከተገኙ ብር 1 ሺህ የሚያስቀጣ ሲሆን፥ ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪ በሚጭኑበት ወቅት በአንድ ሰው 500 ብር የሚቀጡ ይሆናል፡፡

28/01/2022

20/05/2014ዓ.ም
ለክቡራን ተገልጋዮች በሙሉ
በአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቦሌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ተቋርጦ የነበረው
የተሽከርካሪ አገልግሎት የሲስተም ጥገና ስራው የተጠናቀቀ በመሆኑ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን እናሳውቃለን፡፡
የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን

26/01/2022

18/05/2014 ዓ.ም
ለክቡራን ተገልጋዮቻችን በሙሉ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የቦሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የተሽከርካሪ አገልግሎት በሲስተም ጥገና ምክንያት ከዛሬ(18/05/2014 ዓ.ም ) ጀምሮ ላልተወሰኑ ጊዜያት አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን እያሳወቅን የአሽከርካሪ (መንጃ ፍቃድ አገልግሎት ) ግን በስራላይ ይገኛል፡፡ ነገር ግን የተሽከርካሪ አገልግሎት ጥገናው ሲጠናቀቅ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን

02/11/2021

የሰዓት ክልከላውን የሚጥሱ አካላት ከ500 እስከ 6ሺህ በገንዘብ እና ከ1 ወር እስከ 3 ወር መንጃ ፈቃድ በማገድ ያስቀጣል
=================================
(ጥቅምት 20/2014 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ከመጪው ሰኞ ጥቅምት 22/2014 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ነበረበት ይመለሳል፡፡

በዚሁ መሰረት ከሠኞ ጀምሮ በነበረው መመሪያ ቁጥር 03/2011 ተግባራዊ የሚደረገው የከባድ ጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች ክልከላ በሚጥሱ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ከ500 እስከ 6 ሺህ በገንዘብ እና ከ1 ወር እስከ 3 ወር የመንጃ ፈቃድ እገዳ ያስጥላል፡፡

ስለሆነም አሽከርካሪዎች በተለይ የከባድ ጭነት፣ ማሽነሪዎችና መሰል ተሽከርካሪዎችን የምታሽከረክሩ በሙሉ መረጃውን በማወቅ መመሪያውን እንድታከብሩ እናሳውቃለን፡፡

የሚመለከታችሁ የህግ አስከባሪዎችም መመሪያውን በሚጥሱ አካላት ላይ በተቀመጠው የቅጣት ወሰን መሰረት እንዲፈፀም እናሳስባለን፡፡

ለመረጃ ያክል
1. የመንቀሳቀሻ ፈቃድ ሳያወጡ ወይም ሳይዙ በተከለከለ ሰዓት ወደ ከተማ መግባትና በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ እንዲሁም በዋና መንገድ ላይ የጭነት መጫንና ማውረድ ተግባር መፈፀም ለመጀመሪያ ጊዜ 1,000፣ ለሁለተኛ ጊዜ 2,000፣ ከሁለት ጊዜ በላይ ጥፋቱን የፈፀመ 3,000 ብር ተቀጥቶ የአሽከርካሪው መንጃ ፈቃ ለ1 ወር ይታገዳል፡፡

2. ጊዜው ያለፈበት የመንቀሳቀሻ ፈቃድ ይዞ ወደ ከተማ መግባት ወይም በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ ለመጀመሪያ ጊዜ 5,00፣ ለሁለተኛ ጊዜ 1,000፣ ከሁለት ጊዜ በላይ ከሆነ 4,000 ብር ተቀጥቶ የአሽከርካሪው መንጃ ፈቃድ ለ2 ወር ይታገዳል፡፡

3. የመንቀሳቀሻ ፈቃዱን ከተፈቀደለት የሰዓት ክልል ውጭ መጠቀም ለመጀመሪያ ጊዜ 5,00፣ ለሁለተኛ ጊዜ 1,000፣ ከሁለት ጊዜ በላይ 2,000 ብር ተቀጥቶ የአሽከርካሪው መንጃ ፈቃ ለ1 ወር ይታገዳል፡፡

4. የተሰረዘ ወይም የተደለዘ ወይም አስመስሎ የተሰራ የመንቀሳቀሻ ፈቃ ይዞ መገኘት እና መጠቀም፣ እንዲሁም የመንቀሳቀሻ ፈቃን ለሌላ አካ አሳልፎ መስጠት እና ለሌላ ተሸከርካሪ የተሰጠ ፈቃድን እንደራስ አስመስሎ መጠቀም፤ 6,000 ብር ተቀጥቶ አሽከርካሪው መንጃ ፈቃዱን ለ3 ወር ይታገዳል፡፡

5. የመንቀሳቀሻ ፈቃን ከሁለት ጊዜ በላይ መጣል ወይም ማበላሸት፤ 1,000 ብር ተቀጥቶ ክፍያውንም ጭምር በመክፈል ፈቃዱን እንደ አዲስ እንዲያወጣ ይደረጋል፡፡

02/11/2021

ከትላንት ጥቅምት 22 ጀምሮ በአዲስ አበባ የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ የሰዓት ገደብ ክልከላ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል።

የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት መመለሱን ተከትሎ ለአፈፃፀም ይረዳ ዘንድ መመሪያ 03/2011 በመጫን አቅም ልክ መጠን ከባድና ቀላል ተሽከርካዎች በማለት የሰዓት ገደብ ክልከላውን ለይቶ አስቀምጧል፡፡

በመመሪያው መሰረት ማንኛውም የጭነት፣ የማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች ከማለዳ 12፡30 እስከ ረፋዱ 4፡00 ሰዓት እንዲሁም ከቀኑ 10፡00 እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ እንዲሁም ጭነት መጫንና ማራገፍ አይችሉም።

በመመሪያው ክፍል ሁለት ስለሰዓት ገደብ እና ስለፈቃ በሚያትተው ጽሁፍ መሰረት ማናቸውም ቀላል የጭነት ተሽከርካሪዎች ማለትም ከ25 እስከ 35 ኩንታል (ከ2.5 እስከ 3.5 ቶን) የመጫን አቅም ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 12፡30 እስከ ረፋዱ 4፡00 እንዲሁም ከቀኑ 10፡00 እስከ ምሽቱ 2፡00 እንቅስቃሴ የሚገደቡ ይሆናል፡፡

ይህ ማለት ከሰዓት ክልከላው ውጭ ያለው ጊዜ ከረፋዱ 4፡00 እስከ ከቀኑ 10፡00 ድረስ መንቀሳቀስ የሚችሉ ይሆናል፡፡

በተጓዳኙ ከባድ ተሽከርካሪዎች ማለትም ከ35 ኩንታል (ከ3.5 ቶን) በላይ የመጫን አቅም ያላቸው ተሽከርካሪዎች ደግሞ ከማለዳው 12፡30 እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ወደ ከተማ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ እንዲሁም ጭነት መጫንና ማራገፍ እንደማይቻሉ በመመሪያው ተቀምጧል፡፡

የጭነት፣ ማሽነሪዎች እና መሰል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 03/2011 በሰኔ 2011 ዓ.ም ፀድቆ ተግባራዊ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡

11/11/2020

ይህንን ያዉቃሉ!!

የዓለም የጤና ድርጅት ግሎባል እስታተስ የ2018 የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ሪፖርት ዋቢ አድርጎ እንደ ጠቀሰዉ በመንገድ ትራፊክ ደህንነት አማካኝነት ከሚደርሰዉ የሞት አደጋ ዉስጥ በአብዛኛዉ የአደጋዉ ሰለባዎች እግረኞች፣ ሳይክልና ሞተር ሳይክል የሚያሽከረክሩ ናቸዉ፡፡

እነዚሁ ለአደጋ ተጋላጭ ናቸዉ ተብለዉ ከተጠቀሱት ዉስጥ የሞት አደጋዉ ድርሻቸዉ በመቶኛ ሲሰላ
• እግረኞችና ሳይክል የሚነዱት 26 በመቶ፣
• ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች 28 በመቶ፣
• ተሳፋሪዎች 29 በመቶ እንዲሁም ሌሎች 17 በመቶ ይሸፍናሉ፡፡
• ሞተር ሳይክል ለሚነዱት ሰዎች ሄልሜት (የጭንቅላት መከላከያ ቆብ) አድርገዉ እንዲያሽከረክሩ የሚገደዱት በአደጋ ጊዜ የሚደርስባቸዉን ጉዳት መጠን ለመቀነስ ነዉ፡፡
• አንድ ግለሰብ የደህንነት ቆብ በማድረጉ የአደጋ ተጋላጭነትን 42 በመቶ ሲቀንስ በጭንቅላት ላይ የሚደርሰዉንም አደጋ 69 በመቶ ይቀንሳል ይላል ሪፖርቱ፡፡
• አሽከርካሪዉና ከጎኑ ወይንም ጋቢና የሚቀመጡ ተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ በማሰራቸዉ ሊደርስ የሚችለዉን የሞት አደጋ ከ 40- 50 በመቶ የሚቀንስ ሲሆን ከኋላ የሚቀመጡ ተሳፋሪዎች ላይ ደግሞ ሊደርስ የሚችለዉን የሞትና ከባድ የአካል ጉዳትን 25-75 በመቶ ይቀንሳል፡፡
• በተሽከርካሪ ዉስጥ ህፃናትን በህፃናት ማስቀመጫ ወንበር ማስቀመጥ በአደጋ ወቅት ሊደርስ የሚችለዉን የሞት መጠን 60 በመቶ ያህል እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡
• በሰዓት 35 ኪ/ሜ እያሽከረከሩ እግረኛ ቢገጩ ከሞት የመትረፍ ዕድሉ በሰዓት 30 ኪ/ሜ ከሚያሽከረክሩበት ጊዜ ሁለት እጥፍ የበለጠ ነዉና የፍጥነት ገደብዎን ጠብቆ ያሽከርክሩ፡፡
• የመንገድ ትራፊክ አደጋ ከ5 እስከ 29 ዓመት የዕድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙትን ህፃናትን ወጣቶችን በመግደል የአንደኛ ደረጃን ይዟል፡፡ ስለዚህ እባክዎን ራስዎን፣ ቤተሰብዎንና ወገኖን እጅግ አስከፊ ከሆነዉ የመንገድ ትራፊክ አደጋ ይጠብቁ፡፡

Address

አዲስ ከተማ, Chid Tera
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 12:00

Telephone

+251911214410

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መሐመድ ሁሴን ዓመታዊ የመኪና ምርመራ / Mohammed Hussein annual car inspection posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share