የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS

የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS Perform procurement of public organization common user items and nationally strategic utilities; render efficient and effective property disposal service;

የመንግስት ግዥ አገልግሎት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 184/2002 ሐምሌ 2 ቀን 2002 ዓ.ም ሲቋቋም ዓላማዎቹ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚጠቀሙባቸውን ተመሳሳይ ዕቃና አገልግሎቶች እንዲሁም አገራዊ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸው እቃዎችና አገልግሎቶች ከከፍተኛ ግዥ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በሚያስገኝ ተመጣጣኝ ዋጋ፣ በተገቢው ጊዜና በተፈላጊው ጥራት እንዲቀርቡ ማስቻል፣በሽያጭ እንዲወገዱ ውሳኔ የተሰጠባቸውን የመንግስት መ/ቤቶች ንብረቶች በተቀላጠፈ አኳኋን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲወገዱ ማስቻል እና ለመንግስት የልማት ድርጅቶች በዕቃና አገልግሎት ግዥ እንዲሁም በንብረት ማስወገድ ረገድ እገዛ ማድረግ ናቸው፡፡

16/08/2026
13/08/2026

ለአገልግሎቱ ስራ አስፈጻሚዎች እና ለሚመለከታቸው ሠራተኞች በኦንላይን የሙከራ ፈተና ተሰጠ
*****************
ዜና፡ አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 07 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርምን ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት በዛሬው ዕለት 79 ለሚሆኑ የአገልግሎቱ ስራ አስፈጻሚዎች እና የሚመለከታቸው ሠራተኞች በተቋሙ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የስራ ክፍል አስተባባሪነት በኦንላይን የሙከራ ፈተና እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡
የተሰጠው የሙከራ ፈተናም ሠራተኞች ራሳቸውን እንዲገመግሙ እና ዝግጅታቸውን የበለጠ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የረዳቸው መሆኑን ከተፈታኝ ሰራተኞች ጋር በተደረገው ውይይት ለመገንዘብ ተችሏል፡፡

“በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ”  የአገልግሎቱ አመራርና ሠራተኞች ነፃ የጤና ምርመራ አደረጉ*********************ዜና፡ አዲስ አበባ ፡ ነሐሴ 07 ቀን 2018 ዓ.ም  የመንግስት ግዥ ...
13/08/2026

“በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ”
የአገልግሎቱ አመራርና ሠራተኞች ነፃ የጤና ምርመራ አደረጉ
*********************
ዜና፡ አዲስ አበባ ፡ ነሐሴ 07 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው የክረምት የበጎ ፈቃድ ነጻ የህክምና አገልግሎት ከአለርት ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመጣ የህክምና ቡድን በዛሬው ዕለት አጠቃላይ የጤና ምርምራ አድርገዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ፡ አብዛኛው ሠራተኛ አስቦ እና አቅዶ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ መደበኛ የጤና ምርመራ የማድረግ ልምዱ አነስተኛ መሆኑን አንስተው፤ በዛሬው ዕለት ለአመራሮች እና ሠራተኞች የተደረገው ይህ ነጻ የጤና ምርምራ ጠቀሜታው የጎላ እና ሠራተኞች የጤና ሁኔታቸውን እንዲያወቁ የሚረዳ የበጎ ተግባር ስራ ነው ብለዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ለዚህ የበጎ ተግባር ትብብር ላደረገው የአለርት ሆስፒታል እና የህክምና ቡድኑ እንዲሁም ፕሮግራሙን ላመቻቹት በአገልግሎቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ የስራ ክፍል ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የ2017 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ኦዲት የመውጫ ስብሰባ ተካሄደ*********************ዜና፡ አዲስ አበባ ፡ ነሐሴ 06 ቀን 2018 ዓ.ም  የመንግስት ግዥ አገልግሎት የ2017 በጀት...
12/08/2026

የ2017 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ኦዲት የመውጫ ስብሰባ ተካሄደ
*********************
ዜና፡ አዲስ አበባ ፡ ነሐሴ 06 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት የ2017 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸምን ለመገምገም ከመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በመጡ የኦዲት ባለሙያዎች ሲካሄድ የቆየው የኦዲት ሥራ ተጠናቆ የመውጫ ስብሰባ ተካሂዷል።
በስብሰባው የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ላይ የታዩ ጠንካራ ጎኖች እና በቀጣይ መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጓል፡፡
በመውጫ ስብሰባውም የአገልግሎቱን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙን ጨምሮ ሌሎች የአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚመለከታቸው ስራ አስፈፃሚዎች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

ሐምሌ 09  ቀን 2018 ዓ.ም በተከፈተው በጨረታ ቁጥርPPS/NVP-7FBI/11/10/2018 በወጣው ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶች ጨረታ ላይ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ስም ዝርዝር
11/08/2026

ሐምሌ 09 ቀን 2018 ዓ.ም በተከፈተው በጨረታ ቁጥር
PPS/NVP-7FBI/11/10/2018 በወጣው ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶች ጨረታ ላይ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ስም ዝርዝር

ማኔጅመንቱ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያየ**************ዜና፡ አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት የማኔጅመንት አባላት በዛሬው ዕለት በሶስት አጀን...
04/08/2026

ማኔጅመንቱ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያየ
**************
ዜና፡ አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት የማኔጅመንት አባላት በዛሬው ዕለት በሶስት አጀንዳዎች ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡
የአገልግሎቱን የህንጻ እድሳት በሚመለከት ስራውን በሚሰሩ ባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበ ዲዛይን ላይ ገለፃ ከተደረገ በኋላ ውይይት በማድረግ በዲዛይኑ መካተት ባለባቸው እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ሃሳብ እና አስተያየት ተሰጥቷል፡፡ የደብዳቤ የመረጃ ልውውጥን በማዘመን በሲስተም በማድረግ ስራዎችን ለመስራት (e-office letter Management System) ላይ በአገልግሎቱ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የስራ ክፍል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በሌላ በኩል ስትራቴጂክ ዕቅድ፣ ካስኬዲንግ፣ ሪፖርት እና የክትትልና ግምገማ ስርዓትን በሲስተም ማድረግ ላይ ከመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በመጡ ከፍተኛ የሶፍትዌር ልማት ባለሙያ በሆኑት አቶ ኃይሌ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቶ ውይይት ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም በአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር በክቡር አቶ አስማረ ይገዙ ማጠቃለያ እና የቀጣይ አቅጣጫ የተሰጠ ሲሆን፤ የአገልግሎቱ ህንፃ እድሳት ዲዛይን እንደ መነሻ በጥሩ መዘጋጀቱን ገልጸው፤ በዲዛይኑ የሚካተቱ የስራ ክፍሎችም ሆኑ ሌሎች መካተት ያለባቸው ክፍሎች በአግባቡ ተለይተው ተካተው ዲዛይኑ ተስተካክሎ በቀጣይ እንደገና መታየት እንዳለበት አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡
ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ስራዎችን በማዘመን ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ አሰራር መዘርጋት ለአገልግሎታችን ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፤ (e-office letter management system) ላይ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የስራ ክፍል በኩል ለክፍሎች ድጋፍ እየተደረገ ስራው እንዲጀመር፤ በሌላ በኩል ስትራቴጂክ እቅድ፣ ካስኬዲንግ እና ሪፖርት አቀራረብን በሲስተም ተግባራዊ ለማድረግ የስትራቴጂክ እና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የስራ ክፍሎች ከሲስተም አልሚው ጋር በጋራ በመስራት ሲስተሙን የበለጠ ማዳበር እንደሚያስፈልግ በሰጡት አቅጣጫ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

“ተስፋን እንትከል” – በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል ዘመቻ!  *************************ዜና፡ አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገ...
03/08/2026

“ተስፋን እንትከል” – በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል ዘመቻ!
*************************
ዜና፡ አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ከሌሎች ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች ጋር በመሆን፣ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሐሳብ በተካሄደው በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል ዘመቻ ላይ በመሳተፍ አሻራቸውን አኑረዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ እና የመንግስት ግዥ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙን ጨምሮ የገንዘብ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች ተሳትፈዋል። በዚህም አገር በቀል፣ ፍራፍሬ እና የዛፍ ችግኞችን በመትከል የአካባቢ ጥበቃን ከማጠናከር ባሻገር፣ ኢትዮጵያ በመጪው ህዳር ወር የምታስተናግደውን የCOP32 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ስኬት የሚደግፍ ተግባር ተከናውኗል።
የመንግስት ግዥ አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች ባለፈው ሳምንትም በእንጦጦ ፓርክ ከ2,000 በላይ ችግኞችን በመትከል በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያላቸውን ቀጣይነት ያለው ተሳትፎ አረጋግጠዋል።

🌱 “ተስፋን እንትከል” 🌱የአገልግሎቱ አመራሮችና ሠራተኞች የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ **************** ዜና፡ አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም  የመንግስት ግዥ አ...
29/07/2026

🌱 “ተስፋን እንትከል” 🌱
የአገልግሎቱ አመራሮችና ሠራተኞች የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ
****************
ዜና፡ አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሃሳብ በተካሄደው የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በንቃት በመሳተፍ፣ በእንጦጦ ፓርክ ከ2,080 በላይ ችግኞችን በመትከል ለአካባቢ ጥበቃና ለአረንጓዴ ኢትዮጵያ ግንባታ የራሳቸውን አሻራ አሳርፈዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ እንደገለጹት፣ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጭነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ሰባት ዓመታትን በማስቆጠር ኢትዮጵያን አረንጓዴ በማልበስ፣ የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ፣ የምግብ ዋስትናን በማጠናከር እና የኢኮኖሚ ዕድገትን በማገዝ በአገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታይ ውጤት ማስመዝገቡን ገልጸዋል።
በዘንድሮው ዓመትም 8.5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሐይቅ ዳርቻ መርሐ ግብሩን በይፋ ማስጀመራቸውን አውስተዋል፡፡
አቶ አስማረ አክለውም፣ የመንግስት ግዥ አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞችም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን በመደገፍ የዘንድሮውን ጨምሮ በተከታታይ ለሰባት ዓመታት ችግኞችን መትከላቸውን እና የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብና በማሳደግ የአካባቢ ጥበቃን ለማጠናከር የጎላ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ጠቅሰው ለተሳተፉ አመራርና ሠራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

27/07/2026

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS:

Shortcuts

Share