26/12/2022
1. Oil pressure warning light (የዘይት ግፊት ማስጠንቀቂያ መብራት)
የዘይት ግፊት (oil pressure) ማስጠንቀቂያ መብራቱ የሚበራው የሞተርዎ የዘይት ግፊቱ በሚያንስበት ወይም በሚጠፋበት ጊዜ እንዲሁም የዘይት መጠን በጣም ዝቅተኛ በሚሆንበት ጊዜ ነው ነው። በዚህ ጊዜ መኪናዎትን ወደ መንገዱ ዳር
በማውጣት ሞተሩን አጥፍተው በ ዲፕስቲክ በመጠቀም ያለውን የዘይት መጠን መጉደሉን እና አለመጉደሉን ማረጋገጥ ይችላሉ።
oil pressure warning light ሊበሩ የሚችሉባቸው ምክንያቶች
የዘይት መጠን ዝቅተኛ ከሆነ
ዘይቱ የቆሸሸ ከሆነ
ዘይት የሚያፈስ ከሆነ
የዘይት ፓምፕ ላይ ችግር ካለ
የዘይት በጣም
ቀጭን ከሆነ ሊሆን ይችላል።
የዘይት ግፊት ማስጠንቀቂያ መብራት በሚበራበት ጊዜ ምን ማድረግ አለቦት?
የዘይት ግፊት መብራት በሚበራበት ጊዜ መኪናዎን ዳር ይዘው በማቆም የዘይት መጠኖን በ ዲፕስቲክ በመጠቀም ማረጋግጡ መጠኑ ትክክል ከሆነ ዘይት አለመቆሸሹን እና በተጨማሪም ዘይት መፍሰስ አለመፍሰሱን ያጣሩ። ሁሉም ትክክል ከሆነ ችግሩ የ ኦይል ፓምፕ ወይም የግፊት ጠቋሚው ሊሆን ስለሚችል ለ ባለሙያ ያሳዩ።
ስለተሽከርካሪው ተጨማሪ ነገር ሲፈልጉ በቀላሉ ለማግኘት ፔጃችን ላይክ ማድረጎን አይዘንጉ።