12/08/2026
ሰላም ቅዱሳን!
በወላይታ ቀጣና ቃለ ሕይወት ቤ/ክ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያደረገ ሁለንተናዊ ተሐድሶ 2ኛ ዓመት፣ 4ኛ ዙር
ከኪንዶ፣ ከቦሎሶ ቦምቤ፣ ከኪንዶ ኮይሻ እና ከዳሞት ፑላሳ ኅብረቶች የተወጣጡ ከ360 በላይ መጋቢያንና መሪዎች በዚህ የሥልጠና መርሐ ግብር ተሳትፈዋል። ሥልጠናውን በንስሐ በመጀመራቸው እግዚአብሔርን ከልብ እናመሰግናለን።
እንዲሁም ይህንን መርሐ ግብር በማመቻቸትና በመምራት ላደረጉት ድጋፍ የአራቱንም ኅብረቶች መሪዎች ከልብ እናመሰግናለን።
ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን!
ነሐሴ 5/2018 ዓ.ም
ጠረጴዛ ፣ ወላይታ ሶዶ ፣ ኢትዮጵያ