SMART PHONE Center

SMART PHONE Center $10 use internet value/price

18/10/2022

ቀረፋን የመመገብ የጤና ጥቅሞች

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

1. በአንቲ ኦክሲደንት የበለፀገ ነው

ቀረፋ በውስጡ ያዘው አንቲ ኦክሲደንት መጠን ቶሎ የማርጀትን ሁኔታ አንደሚያዘገይ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

2. ለልብን ጤናማነት

ጥናቶች እንደሚሳዩት ከሆነ ቀረፋ ለልብ ሕመም ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሆኑታዎችን ይቀንሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኮሌስትሮል መጠን እንዳይጨምርም የመከላከል አቅም አለው፡፡

3. ስኳር ሕመም

ቀረፋ የስኳር ሕመምን የመከላከል አቅም ስለአለው በደም ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

4. ካንሰርን ይከላከላል

አንቲ ኦክሲደንትን በውስጡ ያዘው ቀረፋ ለካንሰር ተጋላጭነታችንን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል፡፡

5. ኢንፌክሽንን ይከላከላል

የሰውነታችንን በሽታን የመከላከል አቅም የነበረ እንዲሆን ይረዳናል፡፡

6. ለጥርስ ጤናማነት እና ጥሩ የአፍ ጠረን

መጥፎ የአፍ ጠረን እንዳይኖረን እና በአፍ ውስጥ የሚገኙ ሕመሞችን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ የሆነ ሚናን ይጫወታል፡፡

እባክዎ ለወዳጅዎችዎ ያካፍሉ!

ጤና ይሰጥልኝ!

06/08/2022
25/07/2022

ማንችስተር ዩናይትዶች ወጣቱን አጥቂ ቤንጃሚን ሲስኮን የማስፈረም ትክክለኛ ፍላጎት አላቸው

ታማኙ የዝውውር ኤክስፐርት ፋብሪዚዮ ሮማኖ ማንችስተር ዩናይትድ የሬድቡል ሳልዝቡርግ አጥቂ የሆነውን ቤንጃሚን ሴስኮን ማስፈረም እንደሚፈልጉ አረጋግጧል ሮማኖ ሲናገር "ማንችስተር ዩናይትድ የሳልዝቡርጉን ባለተሰጥኦ ቤንጃሚን ሲስኮን በደንብ ያውቁታል እሱ ክትትል ከሚደረግባቸው ተጨዋቾች አንዱ ነው በእውነቱ ጎበዝ ተጨዋች ነው ተብሎ ይታሰባል ነገር ግን የቀረበ ወይም የላቀ ስምምነት የለም

ተጨዋቹን ከማንችስተር ዩናይትድ ውጭ በኒውካስትል ባየርን ሙኒክ ቦሩሲያ ዶርትመንድም ይፈለጋል ስሎቪኒያዊው አጥቂ በሳልዝቡርግ በ38 ጨዋታ 12 ጎል 8 አሲስት አርጓል እንደ ዘ ታይምስ ዘገባ ከሆነ ሲስኮ በኦልትራፎርድ የሮናልዶ ተተኪ ሆኖ አደለም ሚመጣው ሆኖም ተጨዋቹ በቴንሀግ ስር በጊዜ ሂደት ኮከብ ሊሆን እንደሚችል ይታሰባል ወጣቱ አጥቂ ዶርትመንድን የተቀላቀለውን ካሪም አዴይሚ ምትክ ሆኖ በሳልዝቡርግ ይታያል

ለ19 አመቱ ተጨዋች በማንችስተር መፈለግ እጅግ አስደሳች እንደሚሆንለት ይታሰባል ሳልዝቡርጎች ከአጥቂያቸው እስከ £55m ይፈልጋሉ ተጨዋቹን በዚህ አመት ማቆየት ይፈልጋሉ ነገር ግን ገፍቶ ሚመጣ ክለብ ካለ ሊሸጡት ፍቃደኛ ናቸው ኒውካስትሎች ተጨዋቹን ለማስፈረም በተደጋጋሚ ሙከራ አድርገው ነበር ዩናይትዶች ከሲስኮ በተጨማሪም አስቸጋሪውን የአንቶኒን ዝውውር መጨረስ ይፈልጋሉ።

24/07/2022

አዲስ Smart ሞባይል ስልክ ሲገዙ ማገናዘብ የሚገባዎ 13 ነገሮች ከምሳሌ ጋር ~+
መግዛት ያሰቡት smart ሞባይል ስልክ iPhone ወይም Samsung ወይም ሌላ ሊሆን ይችላል።ማንኛውም smart ሞባይል ስልክ ሲገዙ ስልኩ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን 13 መመዘኛዎች ማሟላቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
1~ ፕሮሰሰር(Processor)
ብዙ ግዜ ጌም የሚጫወቱ ከሆነ፣ቪድዮ የሚያዩ ከሆነ ወይም የቪድዮ ኤዲቲንግ የሚሰሩ ከሆነ የስልኩ ፕሮሰሰር Qualcom Snapdragon(652/820/821) ቢሆን ይመረጣል።ለመካከለኛ ተጠቃሚ ፕሮሰሰሩ MedaTek ከሆነ በቂ ነው።
2 ~ ካሜራ
ፎቶ የማንሳት ልምድ ያለው ሰው የስልኩ ካሜራ 13mp(Megapixels) በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።ለመካከለኛ ተጠቃሚ ግን 8mp በቂ ነው።
3 ~ ባትሪ
ብዙ ሰዓት ቪድዮ ለሚያይ፣ጌም ለሚጫወት ሰው ባትሪው 3500mAh(Miliamp Hour) በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ለመካከለኛ ተጠቃሚ 3000mAh በቂ ነው።
4 ~ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS)
የተለያዩ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS) ቨርዥኖች አሉ።ለምሳሌ samsung galaxy ስልኮች ኪትካት፣ሎሊፓፕ፣ማርሽሜሎ...ወዘተ የተባሉ ቨርዥኖች አሉ። ስለዚህ latest ቨርዥን መምረጥ ይመከራል።
5 ~ Storage
ስልኩ በቂ የማጠራቀሚያ አቅም ቢኖረው ይመረጣል። 16GB/32GB/64GB..ከነዚህ ውስጥ መምረጥ ነው። ስልኩ ኤክስተርናል ሜሞሪ(microSD card) የሚቀበል መሆን አለበት።
6 ~ Headphone Jack
HeadPhone 3.5mm audio
jack ቢሆን ይመረጣል።
7 RAM ከተቻለ ከ4GB በላይ ቢሆን ጥሩ ነው ነገርግን ለመካከለኛ ተጠቃሚ 2GB በቂ ነው
8 USB File transfer USB 2.0 በአሁኑ ጊዜ ያለ ስለሆነ ይህ ፖርት ያለው ቢሆ ይነረጣል , USB 3.0 ቢሆን ጥሩ ነው.
9 Physical Size በኢንች ለናንተ የሚቸውንም መምረጥ አለባችሁ በተለይ ለአያያዝ ምቹ መሆኑን አረጋግጡ።
10 የሚቀበለው የሲም ካርድ አይነት መለየት።
11 Display: 6.5 inches በጣም ምርጥ ነው ለአያያዝ ምቹ ነው።
12 Resolution 1080 x 2400 pixels ቢሆን ይመከራል
13 Data 4G LTE ለመጠቀም ያመች ዘንድ 4G Support የሚያደርግ ቢሆን ይመረጣል

ምሳሌ ከታች ያለውን Specification ተመልከቱ።
Dimensions: 75.8 x 164 x 8.9 mm
Weight : 205 g
SoC: MediaTek Helio P35 (MT6765)
CPU : 4x 2.3 GHz ARM Cortex-A53, 4x 1.8 GHz ARM Cortex-A53, Cores : 8
GPU : PowerVR GE8320, 680 MHz
RAM : 3 GB, 4 GB, 6 GB
Storage : 32 GB, 64 GB, 128 GB
Memory cards : microSD, microSDHC, microSDXC
Display : 6.5 in, TFT, 720 x 1560 pixels, 24 bit
Battery : 5000 mAh, Li-Ion
OS: Android 10
Camera : 8000 x 6000 pixels, 1920 x 1080 pixels, 30 fps
SIM card : Nano-SIM
Wi-Fi : a, b, g, n, n 5GHz, ac, Dual band, Wi-Fi Hotspot, Wi-Fi Direct
USB: 2.0, Micro USB
Bluetooth: 5.0
Positioning: GPS, A-GPS, GLONASS, BeiDou
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅ #ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology

13/07/2022
10/07/2022
12/06/2022

ፎረፎር ለማጥፋት የሚረዱ 4 ዘዴዎች

እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች ፎረፎር እንደሚያሰቃያቸው እንገነዘባለን፤ ይህ መረጃም ለሁሉም እንዲደርስ
እንፈልጋለን።

እናንተም ማንበብ ከመጀመራችሁ በፊት ሼር አድርጉት። መልካም ንባብ 🙏🏽

ፎረፎር በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች ይከሰታል።

በተለይም በጸጉር ቆዳችን ላይ የሚገኙ ነጭ የደም ህዋሳቶች ሲሞቱ ነው ፎረፎር የሚከሰተው።

ፎረፎር ፀጉር እንዲያልቅና እንዲበጣጠስ ከማድረጉም በላይ የጸጉር ውበትንና ቆዳን ይጎዳል።

ይሁን እንጂ በተለያዩ መንገዶች ፎረፎርን መከላከል ይቻላል።

1. እርጎ እና በርበሬ

በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው እርሾ በአንዳንድ የሰውነታችን ክፍሎች ላይ መጉረብረብ እና መንተብተብ ይፈጥራል።

ለዚህም እንደ እርጎ ያሉ ጎጂ ያልሆኑ ባክቴሪያዎችን የሚይዙ የምግብ አይነቶችን መጠቀም አይነተኛ መፍትሄ ነው።

ሁለት ማንኪያ የደቀቀ በርበሬ እና 1 ኩባያ እርጎ በመደባለቅ ፀጉራችን የሚበቅልበትን ቆዳ መቀባት እና ከአንድ ሰዓት በኋላ መታጠብ ፎረፎርን ለማጥፋት ትልቅ ድርሻ እንዳለው ይነገራል።

2. እሬት (አሎቬራ)

እሬት ፎረፎርን ለመከላከል በተለይም በኢትዮጵያ ለበርካታ ዘመናት ስንጠቀምበት ኖረናል።

በፎረፎር የተገጎዳ ቆዳን እሬት መቀባት የሞቱ ህዋሳቶችን ከማስወገዱም ባሻገር ለፀጉር እድገት አይነተኛ ሚና እንዳለውም ይታመናል።

3. አፕል

አፕል ለፀጉር እድገት የሚረዳው ፕሮሳይኒዲን ቢ-2 የተባለ የተፈጥሮ ንጥረ ነገር የያዘ መሆኑን ተከትሎ ጤናማ ፀጉር እንዲኖረን ያደርጋል።

ሁለት ማንኪያ የአፕል ጭማቂ ከሁለት ማንኪያ ውሃ ጋር በመቀላቀል መቀባት፤ ከዚያም ከ15 ደቂቃ በኋላ መታጠብ ፎረፎርን ለማጥፋት ብሎም የፀጉር እድገትን ለማፋጠን ይረዳል።

4. ዝንጅብል

ዝንጅብል ለሰውነት መጉረብረብ ወይም መመረዝ የሚያጋልጡ ነገሮችን የሚከላከሉ ንጥረ ነገሮች ይዟል።

ስለሆነም ዝንጅብልን በመላጥና በማድቀቅ ከሰሊጥ ዘይት ጋር በመደባለቅና የፀጉር ቆዳን በመቀባት ፎረፎርን መከላከል ይቻላል።

መልካም ጤንነት!!

ወቅታዊ እና የተሟሉ የጤና መረጃ ለማግኘት፤

ፌስቡክ: https://facebook.com/EthioTena
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/ethiotenadaniel
ቴሌግራም ግሩፕ: https://t.me/ethiotenadgroup
ኢንስታግራም: https://instagram.com/ethiotena
ቲክቶክ: https://tiktok.com/
ዩቲዩብ: https://youtube.com/channel/UCJkUBphmSRDWD2BvZznwFfg

Address

Addis Ababa
[email protected]

Telephone

+251944740862

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SMART PHONE Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to SMART PHONE Center:

Share