Horizon Addis Tyre Manufacturing PLC

Horizon Addis Tyre Manufacturing PLC Proudly Ethiopian! Vision
2025-60-10!!

Mission
HATMPLC Locally develops and manufactures all types of bias and radial tyres which are perfectly compatible to Ethiopia and African countries; by utilizing skillful and experienced professionals and by investing in the advanced technology and supply its output with fair price for the purpose of supporting the transport, farming, manufacturing industry and construction sectors of Ethiopia a

nd the neighboring countries. Being a leading brand in Ethiopia and known in Africa, HATMPLC secures and ensures 60% market share in the local market and 10% of its production volume export to East-African countries in the year 2025 EC.

20/09/2025
ሆራይዘን አዲስ ጎማ ለተማሪዎች ድጋፍ ለማድረግ የመክፈቻ መርሃግብር አዘጋጀ፡፡ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአዲስ መልክ ባዘጋጀው የማህበራዊ ሃላፊነት ፖሊሲ መሰረት...
12/06/2025

ሆራይዘን አዲስ ጎማ ለተማሪዎች ድጋፍ ለማድረግ የመክፈቻ መርሃግብር አዘጋጀ፡፡
ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአዲስ መልክ ባዘጋጀው የማህበራዊ ሃላፊነት ፖሊሲ መሰረት በዩንቨርስቲ እና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ላሉ 10 ተማሪዎች ከማናጅመንቱ ደመወዝ በየወሩ ተቀናሽ በማድረግ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ ገብቷል፡፡ ይህንንም ለማሳወቅ መርሃግብር የተዘጋጀ ሲሆን በዚህም ድጋፍ የሚደረግላቸው ተማሪዎች፤ ባለድርሻ አካላት እና የድርጅቱ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ በዚህም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እየተማሩ ያሉ፤ በድርጅቱ ዙሪያ ከሚገኙ ማህበረሰብ የተመረጡ እና በድርጅቱ ውስጥ እያገለገሉ ከሚገኙ ሰራተኞች ልጆች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተብራቷል፡፡
በተያያዘም ለሰራተኞች እና ለአካባቢው ነዋሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ የልጆች ማቆያ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ እና የሚያስፈልጉት ቁሳቁስ ተሟልተው ወደ ስራ ገብቷል፡፡ በዚህም ለልጆች የማቆያ አገልግሎት፤ የምገባ እና የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
የአካባቢ ነዋሪውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የንጹህ ውሃ መጠጥ የማቅረብ ስራም በድርጅቱ በኩል የተከናወነ ሲሆን በዚህም ነዋሪዎችን ተጠቃሚ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም ለማገዶ የሚሆን እንጨቶች ለአካባቢው ነዋሪዎች አከፋፍሏል፡፡
የሆራይዘን አዲስ ጎማ ማህበራዊ ትስስር ገጾች ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100093044655521
YouTube: https://www.youtube.com/watch?v=kluAG0g-YUA
Telegram:
WhatsApp: https://chat.whatsapp.com/FL1fFwtUUCaFZA22ht31xM

11/06/2025
ሆራይዘን አዲስ ጎማ ለደንበኞቹ የጎማ አያያዝና አጠቃቀምን በተመለከተ ስልጠና ሰጠ፡፡በተሽከርካሪ ጎማ አያያዝና አጠቃቀም ላይ ትኩረት ያደረገ የቴክኒክ ስልጠና ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪን...
11/06/2025

ሆራይዘን አዲስ ጎማ ለደንበኞቹ የጎማ አያያዝና አጠቃቀምን በተመለከተ ስልጠና ሰጠ፡፡
በተሽከርካሪ ጎማ አያያዝና አጠቃቀም ላይ ትኩረት ያደረገ የቴክኒክ ስልጠና ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለደንበኞቹ በ5 ዙር ሰጥቷል፡፡ በዚህም ከመንግስት እና ከግል ድርጅቶች የተሰባሰቡ ሾፌሮች ፤ ጎሚስታ ባለሙያዎች ፤ መካኒኮች ፤ ንብረት ሃላፊዎች እና ግዥ ባለሙያዎች በአጠቃላይ ለ429 ሰራተኞ ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡ ስልጠናው የፋብሪካ ውስጥ ጉብኝት ፤ የቲዎሪ እና የተግባር ስልጠና ያካተተ ሲሆን ስልጠናውም በድርጅቱ የሽያጭ እና ገበያ መምሪያ የስራ ሃላፊዎች እና ከፍተኛ የደንበኞች አገልግሎት ሰራተኞች ተሰጥቷል፡፡ የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ የተወሰደውን ስልጠና ወደ ተግባር በመቀየር ጎማን በትክክለኛው መንገድ በመጠቀም የጎማን የአገልግሎት ዘመን ለመጨመር ፤ ድርጅትንም ሆነ ሃገርን ከብክነት ለመታደግ የሁሉም ሰልጣኝ ርብርብ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል፡፡ ሰልጣኞችም የተሰጣቸውን ስልጠና እና እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር የተቋማቸውን ውጤታማ የሃብት አጠቃቀም አሰራር ለማሳደግ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል፡፡

የሆራይዘን አዲስ ጎማ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100093044655521
YouTube: https://www.youtube.com/watch?v=kluAG0g-YUA
Telegram:
WhatsApp: https://chat.whatsapp.com/FL1fFwtUUCaFZA22ht31xM

05/06/2025

Address

Addis Ababa
SARIS

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Horizon Addis Tyre Manufacturing PLC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Horizon Addis Tyre Manufacturing PLC:

Share